የተመዘገቡትን ድርጅቶች ይደግፉ:: እርስዎ ይግዙላቸው እኛ በነፃ እናደርሳለን:: ድጋፎ ሙሉ በሙሉ ለመድረሱ ማረጋገጫ ከረዱት ድርጅት ያገኛሉ:: ይበልጥ ለማወቅ ከታች ያንብቡ::
- Sun chips 28gBr 30.00 Inc.vat
- Moya biscuitBr 17.00 Inc.vat
- Hand soap 500LBr 95.00 Inc.vat
- OMO hand washing 1kgBr 300.00 Inc.vat
ሙዳይ የበጎአድራጎት ማህበር
ሙዳይ የበጎአድራጎት ማህበር በሕጋዊነት የተመዘገበ የአገር ውስጥ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን በዋናነት ወላጅ አልባ ለሆኑ እና ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ሕፃናት እና ባሎቻቸው በሞት የተለዩዋቸው እና ብቸኛ እናቶች ጋር ይሠራል፡፡ የተመሰረተው በወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ኮተቤ ውስጥ ነው፡፡የሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር ለህፃናት እና ለሴቶች ሁሉን አቀፍ እንክብካቤ እና ድጋፍ በመስጠት የ20 ዓመት ልምድ አለው፡፡ድርጅ አብዛኛውን ወጪ የሚሸፈነው በእህት ቢዝነስ ኩባንያ (ፍሬሽእናግሪንኃ.የተ.የግ.) እና ከአከባቢው ማህበረሰብ እና ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡
ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ህፃናት፤ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞችን ከልመና፤ ከጎዳና ተዳዳሪነት እና ከዝቅተኛ ህይወት በማላቀቅ በራሳቸው እንዲቆሙ ማስቻልን ዋና አላማው በማድረግ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ አገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ማህበሩ በስሩ ከ1000 በላይ ህፃናት እና እናቶችን የያዘ ሲሆን በአላማው መሳካትም ለእነዚህ ተጠቃሚዎቹ መጠለያ በመከራየት፤ ምግብ፤ አልባሳትን እና የሙሉ ጤና ምርመራ አገልግሎትን እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ተጠቃሚዎችን በማህበሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው ትምህርት ቤት ከነርሰሪ እስከ ኬጂ 3 ድረስ በተሟላ መልኩ የነፃ የትምህርት አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድረስ ለሚማሩት ተማሪዎች ሙሉ ወጪያቸው በመሸፈን ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡
ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ይህንን ስራ እያከናወን የሚገኘው ያለምንም ቋሚ ፈንድ እና የወጪ ድርጅት ድጋፍ ሲሆን በጎ አድራጊ ግለሰቦች እና ተቋማት በሚያደርጉት የእውቀት (ሃሳብ) የገንዘብ እና የጉልበት ድጋፍ ነው፡፡ በተጨማሪም አቅሙ ካላቸው ሰዎች የተለያዩ የሙያ ስልጠና በመስጠት ወርሃዊ ገቢ እንዲኖራቸው እና እራሳቸውን ከተረጂነት እንዲያላቅቁ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ህፃናቱም የነገይቱ ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋዎች እንደመሆናቸው ልዩ ትኩረት በመስጠት ትምህርታቸውን እስከ ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ድረስ እያስተማረ ይገኛል፡፡
ቶሎማርት ኢ-ኮሜርስ መድረክ ከሙዳይ የበጎአድራጎት ማህበር ጋር በቀላሉ በመለገስ በማህበረሰብዎ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት በመድረኩ ላይ መሰረታዊ የማኅበሩን ፍላጎቶች ድጋፍ እንዲሰጡ ነፃ መድረክ በማመቻቸት ከሙዳይ የበጎአድራጎት ማህበር ጋር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ የቶሎማርት ኢ-ኮሜርስ መድረክ በመድረኩ በኩል ለሚደረጉ ማናቸውም ልገሳዎችን በነፃ ያደርሳል፡፡
Muday Charity Association
Muday Charity Association is legally registered local NGO which mainly works with Orphan and Vulnerable Children and Widowed and Single Mothers. It was found by Mrs. Muday Mitiku in Kotebe, north of Addis Ababa.Muday Charity Association has 20 years of experience in providing comprehensive care and support for children and women. Basically, most of the cost of the company is covered by the sister business company (Fresh and Green PLC) and good hearted people from the local community and outside of Ethiopia.
Since establishment, it has created several opportunities for more than 1000 women through trainings and job opportunities that enable them to be self-reliant both psychologically and economically. Currently Muday Charity Association is a home for 650 children and youth and 450 mothers. Muday provides comprehensive care and support both for the children and the mothers. These include; shelter (house rent), food, school, health, clothes and so on. The mothers in the center are supported through different skill trainings and will be employed when they qualify.
Tolomart e-commerce platform is working with Muday charity association by providing free gate way of offering support by availing basic needs of the association on the platform so that you can donate easily from your comfort and make a real difference in your community. In addition to providing free advertising platform, Tolomart provides free delivery of products for any donations made through the platform every Friday.
If you like to support us (Muday Charity Association) in kinds and items, please use the tolomart shopping platform and we are listing our needy items for the children and women.
Contact Information
Location: Addis Ababa, Yeka Sub-city, Woreda 11, House No. 225,
P.O.BOX: 190405
Website: https://www.mudayenjera.org
Email: mudaymitiku06@yahoo.com
Contact: 0911718205 Mrs. Muday Mitiku(Founder and Head) 0937989898 Mr. Aster (staff)